የፋሽስት ወያኔ እውነተኛ ባህሪ

የፋሽስት ወያኔ እውነተኛ ባህሪ

(አቻምየለህ ታምሩ)

በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ እውነተኛ ባህሪው ተደብቆ ሳይመነኩስ ቆብ ተጭኖለት በተሰየመበት የመንግስትነት ማዕረግ እየተጠራ ምድሪቷ ከምትሸከመው በላይ ግፍና መከራ በግፉዓን ላይ እየፈጸመ ደልቶች ተዘባኖ እስኪያንገሸግሽን እየገዛ ያለ ሽፍታ ቡድን እንደ ወያኔ የለም። ብዙ ሰው ኢትዮጵያ መንግስት እንደሌላት፤ ህዝቦቿም አገር እንደሌላቸው የተገነዘበ አይመስልም። ይህን አለመገንዘባችን ለወያኔዎች በእጅጉ በጅቷቸዋል። ኢትዮጵያ መንግስት እንደሌላት፤ ህዝቦቿም አገር እንደሌላቸው አለመገንዘባችን በጋራ ተነስተን በወያኔ ጭካኔና ከፋት ልክ የሚሆን ተጋድሎ እንዳናካሂድ አድርጎናል። ዛሬ ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው አራት ኪሎ ቤተ ሽፍታ [ቤተ መንግስት ላለማለት ነው] የሚገኘው ዘርፎ የማይጠግብ፤ ገድሎ የማይሰለቸው፤ የማይነኩና የማይደፈሩ የሚላቸው ሰብዓዊ እሴቶች የሌሉት በዱልዱም የሚያርዱ ነፍሰ በላ የትግራይ ነውረኛ ቡድንና የፋሽስት ጥሊያን አገልጋዮች የነበሩ የባንዳ ልጆች የመሰረቱት የቅሚያ ድርጅት ወይንም ፈረንጆች roving bandit የሚሉት አይነት የሽፍታ ድርጅት ነው። ይህ የትግራይ የሽፍታ ድርጅት ኢትዮጵያውያንን እያስተዳደረ ያለው በስሩ ለሚተዳደሩ ሰራተኞች ምንም ደንታ እንደሌለው ትርፍ አግበስባሽ የቅኝ ገዢ የንግድ ኩባንያ ነው።

የዘረፋው፣ የቅሚያው፣ የግድያውና እየተካሄደ ያለው ጭፍጨፋ ሁሉ ባላባት የሆነውን የትግራይ ሽፍቶች አገዛዝ ልንመረምርበት የሚገባው ለወያኔ ባህሪ የሚመጥን አዲስ ንድፈ ሀሳባዊ መሠረት [theoretical framework] ያስፈልጋል። ይህ የማቀርበው የሽፍታ ድርጅት [roving bandit] ንድፈ ሀሳባዊ መሠረት በአገራችን የተዘረጋውን የትግራይ አፓርታይድ አገዛዝ በመዋቅር ለመረዳት የሚያስችልና አገዛዙ ፍጡር የማታለያ ልብሱን አውልቆ በዓለም ፊት እንደ አዳም ራቁቱን እንዲታይ የሚያግዝ ሊሆን ይችላል።
እንደሚታወቀው ደርግ የሳንድረስትና የሳንሲየር ምሩቃን የመሰረቱት አገዛዝ አይሁን እንጂ አስኳሉ የወታደሮች ስብስብ ነበር። ዛሬ ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ቤተ መንግስት ያለው ዘራፊ ቡድን ግን የሽፍቶች ጥርቅም ነው። የወያኔ ሽፍታነት በተለምዶ [conventionally] የምናውቀው አይነት ተራ ሽፍታነት አይደለም። በተለዶ [conventionally] ሽፍታ እያልን የምንጠራቸው የአገራችን ዱር ቤቴዎችና ጨለመ ተገን አድርገው የሚዘርፉ ሽፍቶች ሰብዓዊነታቸው ጨርሶ የተሟጠጠ አይደሉም። ያገራችንን conventional ሽፍቶች ያላቸው ፈሪሀ እግዚያብሔር፣ ሊሻር የማይችል የሞራል ስልጣኔ፤ የማይነኩና የማይደፈሩ ነገሮች ያሏቸውና የሚወቅስ ኅሊና ባለቤቶች እንደሆኑ እኔም እንዳጋጣሚ እግር ጥሎኝ የትሩፋታቸው ተቋዳሽ ልሆን ችያለሁ።

ከአራት አመት በፊት ነበር። የአስተሪዮ ማርያምን ክብረ በዓል ከእናቴ ጋር ላሳልፍ ከመቀሌ ተነስቼ ወደ ጎጃም እየተጓዝሁ ነበር። ከመቀሌ አዲስ አበባ ረፋዱ ላይ ደረስሁና አመሻሽ ላይ ከአዲስ አበባ ወደ ማርቆስ ለመጓዝ በተለምዶ አባዱላ በሚባለው የሕዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ተሳፈርሁ። ሚኒባሱ ከአዲስ አበባ የተነሳው እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ 12 ሰዓት በመሆኑ አባይ ሸለቆ የደረስነው ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ነበር። እኔ የተቀመጥሁት እንዳጋጣ ጋቢናው ውስጥ ነበር። ሸለቆውን ጨርሰን ከደጀን እንዳለፍን እስካፍንጫቸው የታጠቁ ሽፍቶች መሀል መንገድ ላይ ተሰትረው ጠመንጃቸውን በመደገን መኪናችንን አስቆሙት። ያለንን ሁሉ እንድናራግዝ አዘዙን። ሁላችንም እንጨት ሆንን። ህዝብ አዳም «አለቅን!» እያለ ልቅሶ በልቅሶ ሆነ። ፈጣሪ ጣልቃ ገብቶ አለቃ ገብረ ሀና አባይ በረሃ የያዟቸውን ሽፍቶችን እንዴት እንደሸወዷቸው በልጅነቴ ያነበብሁት ቁም ነገር አዘል ቀልድ በውስጤ አቃጨለ። በህይወቴ ወስኜ ከጋቢናው ወረድሁና ሽፍቶቹን አንድ ነገር ብቻ እንዲስሙኝ ለመንኋቸው። እጅ ወደላይ እያሉ በያቅጣጫው እያንባረቁ ለመስማት ፈቃደኛ ባይሆኑም ከአለቃ የተማርሁትን «መላ!» በሚቆራረጥ ድምጽ ነገርኳቸው።

በመኪናው የያዝነው አስከሬን እንደሆነ፤ በጨለማም ለመጓዝ የተገደድነው አስከሬኑን የምናጓጉዝበት ገንዘብ ቸግሮን ስንለምን ውለን ገንዝብ እንደሞላልን መኪና ፈልገን ጉዞ እንደጀመርን፤ አስከሬኑን የምናሳሽግበት ሳጥን መግዣ የሚሆን ገንዝብ እንኳ ተቸግረን በጋቢ ጠቅልለን በመኪናው ውስጥ እንደጫንነውና አስከሬኑ ወደ ሚያርፍበት ስፍራ በቶሎ ካላደረስነው እንደሚፈርስ፤ ቀባሪ ዘመድም እያለቀሰ የኛን መድረስ እንደሚጠባበቅ ስነግራቸው፤ መርዶው የነሱ የሆነ ያህል በድንጋጤ ደርቀው ቀሩ። መሬት ተከፍታ ብትውጣቸው ሳይመኙ አልቀሩም። ሊገድሉንና ሊዘርፉን ያስቆሙን ሽፍቶች የStockholm syndrome ተገለበጠና ያስተዛዝኑኝ ጀመሩ። ስላስቆሙን አብዝተው ይቅርታ ጠይቀውን አስከሬን ላልኳቸው ሰው «ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ከመርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ» ታድነው ዘንድ ተመኝተው በቀሪው መንገዳችን ባለጀሮቻቸው ስላሉ ችግር እንደማያጋጥመን ደውለው እንደሚነግሩልን ቃል ገብተውልን በሀዘን ተውጠው ተሰነባበትን። በዚህም የጎጃም ሽፍቶች ፈሪሀ እግዚያብሔር፣ ሊሻር የማይችል የሞራል ስልጣኔ፤ የማይነኩና የማይደፈሩ ነገሮች ያሏቸውና የሚወቅስ ኅሊና እንዳላቸው መታዘብ ቻልን።

በልጅነቴ ያነበብኋቸው የአለቃ ገብረ ሃና ቁም ነገር አዘል ቀልዶች ከዘረፋና ከሞት አተረፉን። አለቃ በአንድ ወቅት ከባለንጀሮቻቸው ጋር ሆነ የአባይን በረሀ ሲያቋርጡ ከሩቅ ሊዘርፏቸው ወደነሱ ሲሮጡ የነበሩትን ሽፍቶችን በዘዴ ለማለፍ በአኮፋዳ የያዙትን ጠገራ ብር በነጠላ ጨርቅ ጠቅልለው ጭንቅላታቸው ላይ በመሽከምና አብረዋቸው የሚጓዙ የነበሩ የማያውቋቸውን መንገደኞች እንደዲያቆን ኩታቸውን አጣፍተው የባጥ የቆጡን እንዲያነበንቡ አግባቡና ሽፍቶቹ አጠገባቸው ሲደርሱ «እባካችሁ የያዝነው ታቦት ስለሆነ እንዳይጣላችሁ መንገድ ልቀቁን» ብለው ሲናገሩ ሽፍቶች ሶስት ጊዜ ታቦት ነው የተባለውን ተሳልመው «በቸር ወደ መንበርህ ያግባህ» ብለው እነ አለቃ ከአይን እስኪሰወሩ ድረስ በመቆ ታቦቱን እንዳከበሩት ተቀርጾ በቀረው ታሪካቸው አንብቤያለሁ። አለቃ በዚህ ዘዴያቸው አጤ ምኒልክ የተሰጧቸውን አንድ ቀረጢት ጠገራ ብር ከዘረፋ አድነዋል። በኛ ባህል ከታቦት በተጨማሪ አበሻ ወታደርም ቢሆን ሽፍታ ለአስከሬንና ለሙሽራ የማይሻር ክብር አለው። ጎጃም ያሉ ሽፍቶች ላይ ያየነውም ያንን ነው።

ከትግራይ የመጡት ሽፍቶች ወያኔዎች ግን ጎጃም እንዳገኘናቸው አይነት conventional ሽፍቶች አይደሉም። የትግራይ ሽፍቶች የሆኑት ወያኔዎች ከእግዚያብሔር ጸጋና ከወገን ፍቅር የተለዩ በመሆናቸው ሽፍታነታቸው ኮምኒዝምንና ጥላቻን በአናቱ የደረበ ፈሪሀ እግዚያብሔር፣ ሞራልና የሚወቅስ ኅሊና የሌለበት፤ የማይነኩና የማይደፈሩ ነገሮች የሚባሉ ነገሮችን የማያውቅ ወሮበናለትና ወንበዴነት ነው። የወያኔዎች ትክክለኛ ሰውነት ይህ የማይነኩና የማይደፈሩ ነገሮች የማይታወቁበት፣ ሞራል፣ እሳና ኅሊና የሌለበት አረመኔነት ነው።

ሽፍታ የሚተዳደርበት ደንብም ሆነ ህግ የለውም። ሽፍታ ለቅሚያና ዘረፋ የተደራጀ ገዳይ ቡድን ነው። ባገራችን ነግሰው የነበሩት ወታደሮቹ ደርጎች የአገር አንድነትን፣ ብሔራዊ ጥቅምን፣ ሉዓላዊነትና የሰንደቅ አላማ ክብርን በሚመለከት የጠበቀ ስነምግባር ነበራቸው። የዛሬዎቹ ሽፍቶች ወያኔዎች ግን ሞራልና ስነ ምግባር ስለሌላቸው በዋሉበት ሁሉ ጭካኔ የተሞላበት አፈና፣ ዝርፊያ፣ ቅሚያ፣ ድብደባ፣ ግድያ፣ ወዘተ አለ።
ሽፍቶቹ ወያኔዎች ያስናቋቸው ወታደሮቹ ደርጎች መሪ መሆን ባይችሉም የወታደራዊ ስነምግባር ትምህርት ግን ነበራቸው። አስራ ሰባት አመታት ሙሉ «እናት አገር ወይም ሞት!» በማለት በጦርነት የኖሩት ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ለብሔራዊ ጥቅም፣ ለአገር ሉዓላዊነትና ክብር ሲዋጉ ነበር። ደርጎቹ ስለኢትዮጵያ አንድነት፣ ስለብሔራዊ ጥቅም፣ ስለአገር ሉዓላዊነትና ክብር ሲዋጉ የኖሩት «ከራስ በላይ አገር» በሚል በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት በነበሩ ወታደራዊ ትምህርት ቤቶች ይሰጥ የነበረው ወታደራዊ ስነምግባርና የዘመኑ የአገር ፍቅር ውጤቶች በመሆናቸው ነበር።

ሽፍታ ምንም አይነት ስነ ምግባርም ሆነ ግበረ ገብነት አያውቅምና ወታደርም ሆነ መንግስት ሊሆን አይችልም። ሽፍታ ከጫካ ቢወጣም ጫካው ግን ከውስጡ መቸም ቢሆን ሊወጣ አይችልም። ሽፍታ በውስጡ የአገር ፍቅር ስሜት የሚባል ነገር የለውም። ሽፍታ ሁልጊዜ የሚመራው በጫካ ህግ ነው። ሽፍታ የሚመራበት ህግ፤ የሚገዛበት መርህ የለውም። ሽፍታ ፈጣሪ፣ ህሊና እና እውነት የሚባሉ የሰው ልጅ የቆመባቸውን መሰረቶች አያውቁትም፤ ቢያውቀውም ደንታ አይሰጠውም። ለወታደር ባንዳነት ሞት ነው። ለሽፍታ ግን ባንዳነት ክብር ነው። በዘመነ ደርግ የኢትዮጵያ ወታደሮች ኮዳ፣ ውሀና ጋቤጣ ይዘው ለአገር አንድነት በየበረሀው ሲዋደቁ ሽፍቶቹ ወያኔዎች ግን አገር ለማፍረስ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ሁሉ ወዳጅ ሆነው ኢትዮጵያን ሲውጉ ነበር።

የሽፍታ ዋና ስራና ትልቁ ተግባሩ መዝረፍ፣ መግፈፍ፣ መቀማትና መግደል ነው። ወያኔም እንደሽትፋተቱ የተጋዳላይነት ታሪኩን የጀመረው ባንክና ገዳማትን በመዝረፍ፤ አገድ የሚወዱ አርበኞችን በመግደል ነበር። ሽፍታ በአገር አንድነት ዙሪያ፤ ብሔራዊ ጥቅምን በሚመለከት፤ ስለአገር ሉዓላዊነትና ክብር የሚያውቀው ነገር የለውም። ሽፍታ የአገር መደፈር፤ የክብር መዋረድ ሊገባው አይችልም። ወታደር ግን የአገር መደፈርና የክብር መዋረድ ያንገበግበዋል። ለሽፍታ ግን የሀገር ጉዳይ እና መልካም ስራ ለዘረፋው እንቅፋቶች ናቸው። ሽፍቶች ሲዘርፉ ክፋትን ለመፈፀም የማይፈሩት በሰማይ ያለውን አምላካቸውን ብቻ አይደለም፤ ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ ጐረቤትንም አይፈሩም። ይታዘቡኝ ይሆን? ይጠየፉኝ ይሆን? ብለው አይሳቀቁም፤ የህሊና ልጓምም የላቸውም። ሽፍቶች ከጫካ ወጥተው አካላቸው ቢያምርና ንፁህ ቢለብሱ፤ በአደባባይ ቢውሉ ያው ሽፍቶች ናቸው። ለሽፍታ ነፍስ ማጥፋት፣ እምነት ማጉደል፣ ቅሚያና ዘረፋ የህይወት ጥሪ ነው።
ወታደሮች ከተማሩት ስነ ምግባር የማይሄድ ተግባር ሲያገኙ ደም አፋሾች ናቸው። ደርግ ግፈኛ ስርዓት እንደነበር አለም ያወቀው ጸሀይ የሞቀው ሐቅ ነው። ሆኖም ግን ግፈኛው ደርግ ወያኔን የሚያስንቅበት፣ እንዲፈጸሙ የማይፈልጋቸውና የማይታገሳቸው ወንጀሎች ነበሩት። ሊቀመንበር መንግስቱ ኃይለማርያም «በኢትዮጵያ ባህል» ውስጥ እንዲፈጸሙ የማይፈቀዱትን አንዳንድ መረን የለቀቁ በደሎች ተፈጽመው ሲገኙ ባለሟሎቹን ሳይቀር እስከሞት ድረስ በመቅጣት «ታሪክ» የሰራባቸው ወቅቶች ነበሩ።

የብርሀንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሰራተኛ የነበረችውን የሰባት ወር ነፍሰጡር የረሸናትን ግርማ ከበደ ላይ የተወሰደውን እርምጃና ነፍሰጡር የነበረችዋን የኢህአፓውን አምበል የብርሀነመስቀል ረዳ ባለቤት ታደለች ሀይለሚካኤልን ምህረት ብዙ ሰው የሚያውቃቸው የሊቀመበሩ «ፍትሆች» ነበሩ። ሽፍቶቹ ወያኔዎች ግን ምህረት የለሽ አረመኔ ገዳዮች ናቸው። የትግራይ ሽፍቶቹ ወያኔዎች ባለፈው አንድ አመት ብቻ የሰባት ወር ነፍሰጡር፤ የሶስት አመት ህጻንና የሰባ አመት አዛውንት በግፍ ረሽነዋል፤ መግደላቸው ሳያስን የወደቁትን «ጋኔሎች» ብለዋቸዋል። ዛሬ በአገራችን እየተካሄደ ያለውን አይነት አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ሊወዳደር የሚችለው ከ78 ዓመት በፊት በግራኒያኒ ላይ የተቃጣውን ግድያ ተከትሎ ፋሽስት ጥሊያን በአዲስ አበባ ከተማ ያደረሰው የህጻናት፣ የሴቶችና የነፍሰጡር እናቶች ጅምላ ጭፍጨፋ ብቻ ነው።

ወታደሮች አገር አንድ ያደርጋሉ። ሽፍቶች ግን አገር ያፈርሳሉ። በአፍሪካ በጦርነትም ይሁን በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን የሚወጡ አገዛዞች በአገር አንድነት ዙሪያ ለድርድር የማይቀመጡት ወታደሮች ስለሆኑ ነው። በዚህም የተነሳ በመፈንቅለ መንግስት ስትናጥ በኖረችዋ አህጉር አንዱ ሄዶ ሌላው ሲመጣ የአገር አንድነት ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ አይገባም። የኛዎቹ ገዢዎች ወያኔዎች ፖለቲካውን ለድርድር ሊቀርብ ወደማይችል ጎሰኛነት ለውጠው የዘረኝነት አዋጅ በማውጧት አገር የሚበታትንን ደንብ ህጋዊ ያደረጉት ሽፍቶች ስለሆኑ ነው። ወታደሮች ሁሉን በእኩል ይጠብቃሉ። ሽፍቶች ግን ከአንዱ ነጥቀው ቡድናቸውን ያወፍራሉ። ወያኔ ያደረገው ይህን ነው። ሽፍቶቹ ወያኔዎች ከጎጃም፣ ከጎንደር፣ ከወሎ፣ ከሸዋ፣ ከሐረር፣ ከወለጋ፣ ወዘተ የነበሩ ፋብሪካዎችን፣ የአገልግሎት መስጫዎችንና ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን እየነቀሉ ወደ ትግራይ የወሰዱት ለዚያ ነው።

በሽፍቶች ችሎት ግፍ ፍትህ ነው። ሽፍቶች ህመምተኛ፣ ደካማ፣ አዛውንት፣ ድሀ፣ ወዘተ ለመግደልና ለመዝረፍ ቅንጣት ታህል አያመነቱም። ለሽፍቶች ግብረ ገብነት ፋይዳ የለውም፤ በግፍ ገድለው፤ ዘርፈው ህፃናት ልጆች ጎዳና ቢወጡ፤ አረጋዊያን ያለ ጧሪ ቀባሪ ቢቀሩ፣ ትዳር ቢናጋ፣ ማህበራዊ ስርዓት ቢፈራርስ ደንታ አይሰጣቸውም። እንዲያውም የህጻናትን ማሳደጊያ፤ የአረጋውያንን መጦሪያ ይዘርፋሉ። ወታደሮቹ ደርጎች ያቋቋሙትን የህጻናት አምባ የዘረፉት ሽፍቶቹ እነመለስ ዜናዊ ናቸው። ግብረ ገብነትና ስነምግባር የተማሩት ወታደሮች በተነበኑ ጊዜ ጠመንጃ ታጥቀው ለምነዋል። ሽፍቶቹ ግን ዛሬም ቤተ መንግስት ገብተው ባንክ ዘረፋን እንደ ጀብዱ ያወራሉ። በሽፍቶቹ ዓለም በሌላው መከራና ስቃይ መደሰት አዋቂነት፤ ስኬት፣ አጥቂነትና ማሸነፍ ነው።

ስለዚህ ዛሬ በመንግስትነት በተሰየመው ነውረኛ ቡድን ዝርፊያ፣ ግድያ፣ ንጥቂያ፣ ወዘተ ቢስፋፋ ባህሪያዊ ነው። ባገራችን ላይ እየተካሄደ ያለው በደልና ግፍ፤ ዝርፊያና መከራ፤ ንጥቂያና ግድያ እየተፈጸመ ያለው ሽፍታ በመንግስትነት ተሰይሞ ቤተ መንግስት ስለገባ ነው። ዘመን ቢቀየር፣ አለም ቢያልፍ ሽፍታ ባህሪውን ሊቀይር አይችልም። ሽፍታ የፈለገው ቢሰለጥን ህልሙ መዝረፍ፣ መቀማት፣ መግደል፣ መግፈፍና በክብረ ነክ ነገሮች ክብረ ወሰን መቀዳጀት ነው። ሽፍቶች ህግ ያከብራሉ፣ መብት ይጠብቃሉ ተብሎ አይታሰብም። ዘረፋቸውን የሚፈታተን አለማዊ ህግ ቢኖር እንኳ ሽፍቶቹ የበለጠ መዝረፍ እንዲችሉ አድርገው ይቀይሩታል። ከደርግ ወደ ወያኔ የተደረገው ሽግግር በአገር ጉዳይ ወታደራዊ ግብረ ገብነትና ስነምግባር ከተማሩ መኮንኖች በምን ነገር ከስነ ምግባርም ሆነ ከግብረ ገብነት ጋር ምንም ትውውቅ ወደሌላቸው ተራ ሽፍቶች የተደረገ ውድቀት ነበር። ከወታደሮች ወደ ሽፍቶች በተደረገው የአገዛዝ ሽግግር የሚያኮሩ የነበሩ አገራዊ እሴቶች ሁሉ ተዋርደው፤ ልናፍርባቸው በሚገቡ ወራዳ ተግባሮች ግን የኩራት ምልክቶች ሆነዋል። ይህንን ያስተዋለው ያገራችን ሰው «የሽፍታ ደግ፣ የቁልቋል ዘንግ የለውም» ብሏል።

ባጭሩ ለማለት የፈለግሁ ኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስትነት የተሰየመው ቡድን ከፍብዬ በተለምሁላችሁ የሞራልና የህሊናና ልጓም በሌላቸው እሳ የሌላቸው ሽፍቶች እየተመራ ያለውን አቅምና ጉልበት ሳይቆጥብ ለግድያ፣ ለቅሚያ፣ ለዘረፋና ገፈፋ የሚያውል፤ በእምነትና በቅን ሀሳብ ተገፍቶ ያለፋቸው ክፉ ነገሮች በመብራት ተፈልገው የማይገኙለት፤ በትምህርት ተወልደው መልካም የሚሰሩና ለወገናቸው የቢያስቡ ሰዎችን በማጥፋት ክብረወሰን የተቀዳጀው የትግራይ ሽፍቶች የአርታይድ አገዛዝ ነው።
የወያኔን ፋሽታዊና አፓርዳይዳዊ አገዛዝ የመንግስትነት ልብሱን አውልቀን በዓለም ፊት ራቁቱን ስላላቆምነው የትግራይ ሽፍቶች በመሰረቱት የአፓርታይድ አገዛዝ ክፋትና ጭካኔ ልክ የሚመጥን ጸረ ፋሽስትና ጸረ አፓርታይድ ትግል ልናደርግ አልቻልንም።

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን በዘር ላይ የተመሰረተውን ባሪያ አሳደሪ አገዛዝ በሚገባ የሚገልጸው ነጭ ደብቡ አፍሪካውያን በዘራቸው ተመክተው ያራምዱት የነበረውና ሊሰበር የማይችል የኢኮኖሚና የስርጭት ልዩነት ያነበረው የአፓርታይድ አገዛዝ ብቻ ነው። የወያኔን የግፍ ዘመን ያራዘመው በቆዳ ቀለም አንድ ስለሆንን የአፓርታይድ አገዛዝ አራማጅነቱ ሪቁን አለመውጣቱ ነው! የወያኔን አገዛዝ የአፓርታይድ አገዛዝ ነው ስንል የወያኔዎች የአይን ቀለም ስላላማረን ሳይሆን በአገዛዝዝቸው የአፓርትይድ መገለጫ ባህሪዎች ሞልተው ስለፈሰሱ ነው።

የአገራችን አፓርታይድ አገዛዝ አራማጆች ከትግራይ የበቀሉት ወያኔዎች የወርቅ ዘር በሚሉትና በሌላው ኢትዮጵያዊ መካከል ያለው የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና የስርጭት ልዩነት በደቡብ አፍሪካ ነጮችና ጥቁሮች መካከል ያለው አይነት የሰማይና የምድር ልዩነት እንዲፈጠር ኤፌርት የሚባል በመቶዎች የሚቆጠሩ ግዙፍ ኪባንያዎች ያሉት የቅሚያና የዘረፋ ኮርፖሬሽን አቋቁመዋል።

ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የነበረው የአፓርታይድ አገዛዝ Petty Aparthied እና Grand Aparthied በሚባሉ ሁለት መገለጫዎቹ ይታወቅ ነበር። Petty Aparthied የሚባለው በህዝባዊ መገልገያዎችና መዝናኛዎቹ ይታይ የነበረውን የነችጮና የጥቁሮች segregation የሚያሳይ ሲሆን Grand Aparthied የሚባለው ደግሞ በዘር ላይ የተመሰረተውን የቤት ልዩነትና የስራ እድል መድሎ ነው።

የኤርምያስ ለገሰን «የመለስ ልቃቂ» መጽሀፍ ላነበበ በኛ አገር «የወርቅ ዘር ነን» በሚሉ የትግራይ ሽፍቶችና በደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ አራማጅ ነጮች መካከል ያለው ልዩነት የቀለም ካልሆነ የድርጊትና የአስተሳሰብ ልዩነቶችን ፈልጎ ሊያገኝ አይችልም። Petty Aparthied የሚባለው የአፓርታይድ መገለጫዎች ኤርምያስ ለገሰ በ«መለስ ልቃቂት» መጽሀፉ የመጀመሪያ ምዕራፍ ከገጽ 13-37 በወያኔና በሎሌዎቻቸው መካከል ያለውን ልዩነት አስነብቦናል።

ባገራችን ላለው Grand Aparthied ለሚባለው የአፓርታይድ አይነት መገለጫ ደግሞ ዘራችን ከዘራችሁ፤ ደማችን ከደማችሁ ይበልጣል በማለት በዘር ተደራጅተው አገር እየገፈፉ የሀብትና የሁሉ ነገር ጌቶች ስለሆኑት ወያኔዎች በትግራይ ህዝብ ዘንድ የተሰጣቸውን ስም ማንሳት በቂ ነው። ከአስራ ሁለት አመታት በላይ በኖርሁባት በመቀሌ ከተማ ሁለት የመኖሪያ መንደሮች አሉ። አንደኛው ከመቀሌ ከተማ በስተ ምዕራብ አንድ ክፍለ ከተማ ያካለለ ሲሆን ቀደም ሲል «የሙስና መንደር» በሚል ይጠራ የነበረ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ እያንዳንዱ የሙስና መንደር ግቢ ሲገባ የቆሙትን እጅግ ውድ መኪኖች፣ እየተሰሩ ያሉትን አውሮፓና አሜሪካን lavish mansions የሚባሉ አይነት አዳዲስ ቤቶችን በአንድ ክፍለ ከተማ ሙሉ መንጣለላቸውን የተመለከተው ኗሪ «ሆሊውን መንደር» ብሎ ይጠራዋል።

ሁለተኛው የመኖሪያ መንደር ደግሞ ከመቀሌ ከተማ በስተ ምስራቅ የሚገኝ የወያኔዎች ሰፈር ሲሆን ይህንን መንደር ኗሪው በትክክለኛ ስሙ «የአፓርታይድ መንደር» እያለ ይጠራዋል። በአፓርታይድ መንደር የሚጠጣው የባንቧ ውሀ ሳይቀር ከሌላው የከተማዋ አካባቢ የተለየ ነው። እንደ ሆሊድውን መንደር ሁሉ የአፓርታይድ መንደርም ወያኔዎችና ዘመዶቻቸው ተነጥለው ብቻቸው ለመኖር የሰፈሩበት እጅግ ውድና lavish mansions በሚባሉ ቤቶች ያሸበረቀ የአፓርታይዱ አገዛዝ እድምተኞች መንደር ነው። አዲስ አበባ ውስጥ ቦሌ ክፍለ ከተማና 22 ማዞርሪያ የተሰሩ እጅግ ቅምጥል የሆኑ mansions የሞሉት «መቀሌ መንደር»ም የትግራይ አፓርታይድ አገዛዝ አራማጆች ርስት ነው። በመቶሺዎች የሚቆጠሩ የኤፌርት ሰራተኞች ከሌላው ኢትዮጵያዊ አንጻር ቢያንስ ከአምስት እጥፍ በላይ ተከፋዮች እንደሆኑ እኔ በግሌ አውቃለሁ። ከሌላው ኢትዮጵያዊ አንጻር ኤፌርት የፈጠረው ይህ የስራ እድልና ገቢ ልዩነት Grand Aparthied ለሚባለው የወያኔ አፓርዳይድ አገዛዝ መገለጫ ነው።

ስለዚህ የወያኔ አገዛዝ የትግራይ አፓርታይድ አገዛዝ ነው። ይህንን እንጅ ክፉ የአፓርታይድ አገዛዝ በስሙ ልንጠራው ይገባል። ባልዋለበት የመንግስትነት ማዕረግ መጥራት ማቆም አለብን። ቤተ ሽፍታ ያለውን የወያኔ አገዛዝ በትክክለኛ ስሙ የትግራይ የአፓርታይድ አገዛዝ ተብሎ መጠራት አለበት። ይህ አገዛዝ የሰው ተፈጥሮ የለውም። በዚህ የገፈጥሮው እየተመራ እኛን ይጎዳል ብሎ ካሰበ ማንኛውንም ርኩስ ነገር ለማድረግ የአቅም ማነስ ከሚገታው በቀር ሌላ መግቻ ሳይኖረው እስከመጨረሻው ይወጋናል። ስለዚህ ትግላችን ከጠላታችን ተፈጥሮ ጋር የተመጣጠነ መሆን አለበት። ይህንን የጠላታችንን ተፈጥሮ ለወገኖቻችን እናስረዳ። ጠላታችን ተራ አምባገነን አይደለም። በመንግስትነት የተሰየመው የአረመኔ ሽፍቶች የአፓርታይድ አገዛዝ ከፋሽስት ጥሊያን በላይ የከፋ፤ ክፋትና ጭካኔ በኛ ላይ ለመፈጸም የአቅም ማነስ ከሚገታው በቀር ሌላ መግቻ የሌለው አረመኔ ቡድን መሆኑን እናሳውቅ። ይህ መሆኑ ጸረ ፋሽስት ጸረ አፓርታይድ ትግላችን በጠላታችን የክፋት መጠን እንዲሆን ይረዳል። በፈሪሀ እንግዚያብሔር፣ በይሉኝታና በኅሊና ልጓም ተሸብበን ፋሽስቱን የትግራይ አፓርታይድ አገዛዝ መታገል መሞከር «በግ ካራጁ ኋላ እንደሚጎተት» ነው፤ ብዙ ዋጋ ያስከፍለናል!

Share this post

8 thoughts on “የፋሽስት ወያኔ እውነተኛ ባህሪ

Comments are closed.