ማስታወቂያ – በምእራብ አውስትራሊያ የዳግማዊ መዐሕድ የድጋፍ ድርጅት ኮሚቴ

በምእራብ አውስትራሊያ የዳግማዊ መዐሕድ የድጋፍ ድርጅት ኮሚቴ

ውድ ወግኖቻችን፡-

የአማራው ህብረተሰብ መጠነ ሰፊ የሆነ የዘር ማጥፋትና ማፅዳት ወንጀል ተከፍቶበት ህልውናው እጅግ አደገኛ በሆነ ሁኔታ ይገኛል። በመሆኑም የወገኖቻችን ህልውና ለመታደግና ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለው ሁለገብ ትግል ለማገዝ ከዳግማዊ መዐሕድ ጎን በመቆም ታሪካዊ ሀላፊነታችን ለመወጣት እኛ በአውስትራልያ የምንገኝ አማራ ኢትዮጵያውያን እራሳችን እያሰባሰብን እንገኛለን።

ከዚሁ ጋር ተያይዞም በም ዕራብ አስትራሊያ ጊዚያዊ የዳግማዊ መዐሕድ የድጋፍ ኮሚቴ ተቋቁሞ አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ በማድረግ ላይ ይገኛል። ኮሚቴው ከአማካሪዎቹ  ጋር ታህሳስ 11 ቀን 2016 ባደረገው ስብሰባ አጠቃላይ ህዝባዊ ውይይት ሊደረግ የሚችልበትን መድረክ በሶስት ሳምንታት ውስጥ አዘጋጅቶ ሕዝቡን ለማነጋገር በሙሉ ድምፅ ወስኗል። በእለቱም ህዝብ ታግለው ያታግሉናል ብሎ የሚያምንባቸው የዳግማዊ መዐሕድ ቋሚ የድጋፍ ኮሚቴ አባላትን በነጻነትና ፍህታዊ በሆነ አሰራር መርጧል።

የውይይት ቀን፣ ሰዓትና ቦታ ተቆርጦና ተወስኖ እስከሚገለጽ ድረስ ማንኛውንም አይነት ጥያቄም ሆነ አስተያየት ያላችሁ ወግኖቻችን በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች በመደወል መርጃ የምታገኙ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን።

Contacts

04 012 52 795        04 110 67 692       04 212 24 005
04 225 81 302        04 212 46 999      04 786 59 775

ድል ለአማራው ህዝብ!
ዳ/መዐሕድ በምዕራብ አውስትራሊያ

 

 

Share this post