የምስክር ወረቀት

የሰማዕቱን የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ፈለግ በመከተል ለዐማራው ሕዝብ ህልውና፣ መብት እና
እድገት የመላው ዐማራ ሕዝብ ፓርቲ (መዐሕፓ)፣ በአገር ደረጃ ለብዙ ጊዜ ያልተቆጠበ ጥረት
ሲያደርግ ቆይቶ ሕጋዊ ተክለሰውነት ማግኘቱ የተሻለ ሁኔታ እንደሚፈጥርለት አያጠራጥርም። ብዙ
ተግባራዊነትን የጠየቀ እውቅና በመሆኑ ለትግሉ የመጀመሪያ እርከን ነው።

ድርጅቱ ለአንድነትና ለተባበረ ትግል ከዳግማዊ መዐሕድ እስከ መዐሕድ ከዚያም እስከ መዐሕፓ ድረስ
ያደረው መስዋዕትነት ቀላል አልነበረም። ብዙ ትምህርት ተቀስሞበታል።
መላው የዐማራ ሕዝብ በሃገሩ የዜግነት መብቱን ተገፎ፣ ህልውናው ለአደጋ ተጋልጦ እድገቱ ከተቀጨ
ብዙ አስር ዓመታት አልፈዋል። ይህ ከባድ ችግር የሁላችንንም መተባበርና መደጋገፍ ይጠይቃል።
ከመዐሕፓ ጋር ወደፊት!
ድል ለመላው ዐማራ ሕዝብ!

Share this post

14 thoughts on “የምስክር ወረቀት