በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከመዐሕፓ የተሰጠ መግለጫ ፣ አርብ ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ቁጥር፡ መዐሕፓ/003/2011                                                                 ቀን፡ ፳፩/፲/፳፻ዓ.ም

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከመዐሕፓ የተሰጠ መግለጫ

አርብ ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

 

 

ቅዳሜ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ እና በአዲስ አበባ የተከሰተው ክስተት በእጅጉ አሳዛዥ ነው፡፡ በተለይ ባህር ዳር በወንድሞቻችን ላይ የተፈጸመው ግድያ የዐማራን ህዘብ በእጅጉ ያሳዘነ ነው፡፡ ይህ የዐማራ ሕዝብ ፍጅት ቀጣይ ክፍል የሆነ ድርጊት የዐማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጸመው ዕልቂት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መምጣቱን የሚያስረዳ ነው፡፡ ይህ ድርጊት ከፍተኛ ዝግጅትና ጥንቃቄ የተደረገበት ብዙ ዓላማ ያዘለ ፀረ-ዐማራ የሆነ እንቅቃሴ ነው፡፡

ከዓላማዎቹ አንዱ ምልክት የነበሩትን ሰዎች በተለያየ መንገድ እንዲያጣ የተደረገው የዐማራ ሕዝብ መሪዎቼ የሚላቸው እና ምልክት እየሆኑ የመጡ መሪዎች ሲመጡ እነሱን በመግደል ህዝቡን መሪ ማሳጣት ሲሆን ይህም ኩነት በተመሳሳይ ሴራ የተሰውትን ታላቁን የዐማራ ሰማዕት ክቡር ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስን እንድናስታውስ አድርጎናል፡፡  ይህ ፀረ-ዐማራ ግድያ መፈፀሙ ሳያንስ ሁኔታውን በወንድማማች መካከል እርስ-በርስ የተደረገ በማስመሰል ጉዳዩን አንድም ዐማራውን በሀሳብ ለመከፋፈል ብሎም ህዝቡን በጎጥ ለመከፋፈል የተደረገ ዕኩይ ተግባር መሆኑ ነው፡፡ የነዚህ ኃይሎች እንቅስቃሴ ይህን ክስተት በመጠቀምና ሰበብ በማድረግ አስቀድመው ያሴሩባቸውን የዐማራ ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስቶች እና ተሟጋቾች ማሰር፣ ማንገላታት፣ ማሸማቀቅ እና መግደል ሁለተኛው ጉዳይ ሲሆን፤ ይህንንም ካደረጉ በኋላ ለዐማራ የሚቆሙ ታጋዮችን ወይም ድርጅቶችን ጨርሶ ለማጥፋት ወይም በእጅጉ ለማዳከም የታለመ እንደሆነ እናምናለን፡፡ እነዚህ ኃይሎች ይህም ሳይበቃቸው በተደጋጋሚ በግልጽ የምናውቀውን ዐማራው በብዛት የሚኖርበትን “የዐማራ ክልል” የጦርነት አውድማ በማድረግ  ህዝቡን አስከተቸቻላቸው ድረስ እርስ-በርስ ተዋግቶ እንዲጠፋፋ ካልሆነም እነዚሁ ኃይሎች ክልሉን በይፋ ለመውረር የሚደረግ ዝግጅት መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ በነዚህ ሁሉ ድርጊቶች የሥነ-ልቦና ጫና በማድረስ ዐማራን እንደሕዝብ አንገት ለማስደፋት ቀጥሎም ክልሉን ለመቆጣጠር እና ለመበዝበዝ ዓላማ እንዳለ እንገነዘባለን፡፡ ………..read in PDF AAPP Press Release on 28.06.2019-V2

Share this post

6 thoughts on “በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከመዐሕፓ የተሰጠ መግለጫ ፣ አርብ ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ