ከመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) በአትያጵያ አገራችን ውስጥ በዐማራው ህዝብ ላይ እየተካሄደ ስለ አለው ህገወጥ የወረራ ጦርነትን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ።

በአክራሪው ኦነግና በሌሎች ጽንፈኛ ሃይሎች በዐማራ ሕዝብ ላይ የተከፈተው ጦርነት በአስቸቋይ መቆም ይኖርበታል።
ሰፊው የዐማራ ሕዝብ ለዘመናት የኢትዮጵያን ነጻነትና ሉዐላዊነት ለማስከበር ውድ ህይወቱን እየገበረ ለትውልድ ባቆያት አገር ላይ ዛሬ እንደባይተዋር ተቆጥሮ በአክራሪ ጎጠኞች የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመበት ይገኛል። እነዚህ ታሪካዊ የዐማራ ሕዝብ ጠላቶች ሲመቻቸው በጋራ አለበለዚያም በተናጠል ላለፉት አርባ ዓመታት በዐማራው ሕዝብ ላይ ኢሰብዓዊ ጥቃት መፈጸማቸውን አላቆሙም። የዐማራውን ሕዝብ ለማጥፋት የተቀነባበረው የእልቂት ዘመቻ በአስቸኳይ ካልቆመ ይህ በአጠቃላይ በሃገሪቱ ሊያስከትል የሚችለው የጥፋት መዘዝ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ወደማያባራ የርስበርስ መተላለቅ የሚያመራ እንደሆነ ከወዲሁ መገመት ይቻላል።
ከሃያ ሰባት ዓመት የህውሃት ፈላጭ ቆራጭነት ተላቆ ወደተሻለ የለውጥ ምዕራፍ ለመሸጋገር በተደረገው ሕዝባዊ አመጽ የዐማራው ሕዝብ ከኦሮሞ ወንድሞቹ ጋር የትግል አጋርነት በመፍጠር ለውጡ ስኬታማ እንዲሆን ከፍተኛውን መስዋዕትነት ከፍሏል። ነግር ግን ይህ የሕዝባዊ ትስስርና የትግል አንድነት ያስደነገጣቸው ሃገር በቀልና የውጪ ጠላቶች በተቀነባበረ ሴራ የዐማራውንና የኦሮሞውን ሕዝብ አጋጨቶ ለማለያየት በከፍተኛ ደረጃ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። በሰሞኑ በአክራሪ የኦነግ ሃይሎችና በሌሎች ጽንፈኞች በተተለያዩ አቅጣጫዎች በዐማራ ሕዝብ ላይ የተከፈተው መጠነ ሰፊ የእልቂት ጦርነት በከሚሴ ወሎ፣ በሸዋ በአጣዬ፣ በማጀቴና በኤፍራታ ዐማሮች ላይ እየተካሄደ ያለው የጅምላ ጭፍጨፋ በይፋ ያሳያል። መንግሥትም ይህን የአክራሪዎች ወረራና እያደረሱ ያለውን ኢሰብዓዊ የጥፋት ዘመቻ ለማስቆም ብሎም ዜጎችን ከዚህ እልቂት ለመታደግ ደራሽና ውጤታማ እርምጃ በወቅቱ አለመውሰዱ ቅሬታን ከመፍጠሩም በላይ ለትውልድ የሚሸጋገር የታሪክ ጠባሳ ጥሏል።
ውድ የዐማራ ሕዝብ ሆይ፤
በማንነትህ ላይ ባነጣጠረ የጥላቻና የዘር ማጥፋት ዘመቻ ልጆችህ እየተገደሉ፣ ቤተሰብህ እየተበተነ፣ እትብትህ በተቀበረበት ቀየህ፣ ያመረትከው ሰብልህ በእሳት እየጋየ፣ አጽመዕርስትህን ለቀህ እንድትሰደድ፣ የመከራና የግፍ ጽዋን እንድትጎነጭ ተበይኖብሃል። በነዚህ ከሃዲዎች የተከፈተብህ ጦርነት የሚያባራው በራስህና በልጆችህ አንድነትና ቆራጥነት ብቻ እንደሆነ ተገንዝበህ አንተም እንደ አያቶችህ ጠንካራ አንድነት መስርተህ ዘርህንና ትውልድህን ለማዳን ቆርጠህ ስትነሳ ብቻ ነው ።
በዐማራ ሕዝብ ላይ ዘርን መሠረት ያደረገ በጅምላ እየተፈጸመ ያለውን እልቂት ፣ ስቃይ፣ እንግልት፣ መከራና ሞት መዐሕድ በአጽኖት ይኮንናል ፡ ያወግዛል።
ድል ለዐማራ ሕዝብ!
የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ)
read in pdf ….AAPO pres release on the war of aggression launched by OLF terrorist groups

Share this post