የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) የደብረታቦር ሕዝባዊ ስብሰባ በደማቅ ሁኔታ ተጀመረ

የመዐሕድ ስም ሲጠራ እንባ የሚቀድመውን ሕዝብ ከደብረ ብርሃኑ ስብሰባችን በኋላ እናገኘዋለን ብለን አላሰብንም ነበር።

ደብረታቦር ላይ የሚታየው የሕዝባችን ስሜት ተጠፋፍተው የቆዩ ቤተሰቦች ሲገናኙ የሚታየውን አይነት ይመስላል። ሕዝባችን ለአባት ድርጅቱ የሚያሳየው ስስትና ጥልቅ ፍቅር ልዩ ስሜትን ይጭራል። ቁጭት፣ እንባ የተቀላቀለበት ደስታ፣ ሐዘን ብቻ ድብልቅልቅ ያለ ስሜት በአዳራሹ ውስጥ ሰፍኗል። የአባት ድርጅታችን የቀድሞ አባላትና የሰማዕታት ቤተሰቦች በአዳራሹ ተገኝተው ያለፈውን ትውልድ ከአዲሱ የመዐሕድ ትውልድ ጋር የሚያገናኘውን የታሪክ ድልድይ እየገነቡት ነው።

Share this post