ሕዝባዊ የስብሰባ ጥሪ ለደብረ ታቦርና አካባቢው ነዋሪዎች !

የሕዝባዊ ስብሰባ ጥሪ ለደብረታቦር ከተማና አካባቢው ዐማራ ሕዝባችን ብልሁ ዐማራ፣ አንዴ ከመናገርህ በፊት ሁለት ግዜ አስብ፣ አስር ግዜ ለክተህ አንድ ግዜ ቁረጥ እንዲል፣ የታላቁ ሰማዕት መሪያችን ፕሮፌሰር አስራትና የትግል አጋሮቻቸው መራር ተጋድሎ ፍሬና የትውልዱ አደራ የሆነው አባት ድርጅታችን የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት/ መዐሕድ፣ ማህበረሰብን ያሳተፈ የድርጅት ፕሮግራምና እቅድ ክለሳ ስራ ላይ ሰፊ ጥናት፣ ምክክርና ውይይት ሲያደርግ ከቆየ በኋላ የትግል ቅብብሎሽ ዱላውን ከአባቶች ተረክቦ አእላፍት አባላቱ የተሰዉለትን ራዕይ ከዳር በማድረስ አደራቸውን ሊወጣ፣ ዛሬም እንደ ትናንቱ የዐማራ ሕዝብ አለኝታነቱንና የጭንቅ ግዜ ደራሽነቱን ሊያረጋግጥ እንሆ በቁርጠኝነትና በወኔ እንቅስቃሴ ጀምሯል:: በዚሁ መሰረት የእንቅስቃሴ አድማሱን በማስፋት ነገ እሁድ፣ ኅዳር 9 ቀን 2011 ዓ.ም. ፣ የውብ ባህል መገኛና የጀግኖች ዐማሮች መፍለቂያ በሆነችው ደብረታቦር ከተማ ሕዝባዊ ስብሰባ ስለሚያደርግ የከተማውና አካባቢው ነዋሪዎች፣ የድርጅታችን አባላት እና ደጋፊዎች እንድትሳተፉ በአክብሮት ተጋብዛችኋል:: በዕለቱ ኮሎኔል አለበልን ጨምሮ የመዐሕድ ከፍተኛ አመራሮች የሚገኙ ሲሆን፣ የአንድ ትውልድ ዘመን የተሻገረው የድርጅታችን እንቅስቃሴና ቀጣይ ዕቅዶች ለውይይት ይቀርባሉ::

የስብሰባ ቦታና ሰዓት : ዳግማዊ ቴዎድሮስ አዳራሽ፣ ከጠዋቱ 3 ሰዓት

ፈለገ አስራት የትውልዱ ቃል ኪዳን ነው !
የዐማራ ሕዝብ ትግል ያሸንፋል !

Share this post