የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) አመራሮች አዲስ አበባ ገብተዋል። ደማቅ አቀባበልም ተደርጎላቸዋል።

የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐህድ) አመራሮች አዲስ አበባ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል Aug 23 2018

የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መአህድ) አመራሮች አዲስ አበባ ገብተዋል። ደማቅ አቀባበልም ተደርጎላቸዋል።

“የአማራ ህዝብ ለአማራ ብሄርተኝነት እዚህ መድረስ የታገሉ አመራሮቹን ለመቀበል ዶፍ ዝናብ አያግደውም። በዛሬው እለት የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት አመራሮች ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከፍተኛ አመራሮች፣ የድርጅቱ አባላትና የአማራ ብሄርተኛ ወጣቶች በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ተገኝተው የዳግማዊ መአህድን ልዑክ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል!

የድርጅቱ አመራሮች፥ “በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ያለውን ለውጥ በመመልከት በውጭ ሀገር የአማራን መብት ለማስጠበቅ ስናደርገው የነበረውን ትግል በሀገር ውስጥ አጠናክሮ ለመቀጠል ወደ ሀገር ቤት ገብተናል” ብለዋል።

“ከአማራ ክልል መንግስትና ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጋራ እንሰራለን” ሲሉም ተናግረዋል። #ብአዴንን ወክለው አቀባበል ያደረጉላቸው የንግድ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እና የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር አቶ ጃንጥራር አባይ ናቸው። ሚኒስትሩ አቶ መላኩ ብአዴን የክልሉን የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ ከሀገር ውጭና በሀገር ውስጥ ካሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመስራት የጀመረውን ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የዳግማዊ መአህድ እና የአብን አመራሮች ከቦሌ ወደ ስላሴ ካቴድራል በመሄድ በፕሮፌሠር አሥራት ወልደዬስ ሀውልት ላይ የአበባ ጉንጉን አሥቀምጠዋል።

ይህ ለአማራነት የተከፈለ የምንሰጠው ዋጋ ነው። የአማራ የሆነን ሁሉ ስናከብር አማራነት ከፍ ይላል። አማራዊ አንድነት ይጠናከር ይደራጅ!!!
..
✔ በኢትዮጵያ በሚኖራችሁ ቆይታም ከተለያዩ አማራዊ ሃይሎች ጋር በአማራ ህዝብ ትግል ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት በማድረግና አማራዊ አንድነቶችን በማጠናከር ረገድ ለህዝባችን የሚጠቅምና ትግላችንን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሳድግ ስራ እንደምትሰሩ እምነቴ ነው። የምንይልህ አምላክ ከናንተ ጋር ይሁን!

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ
ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ የሚለውን መርሃችንን በተግባር ይገለጥ!!!

[አቢሶሎም ፍቅሩ እንደከተበችው] እና  የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ከዘገበው ሪፖርት የተወሰደ
#ድል_ለአማራ_ህዝብ!!!”

የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐህድ) አመራሮች አዲስ አበባ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል Aug 23 2018
የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐህድ) አመራሮች አዲስ አበባ ሲገቡ የተደረገላቸው አቀባበል Aug 23 2018

Share this post