መዐሕድ ለጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በአካል ሊያቀርብ የነበረውና በሰዓት እጥረት ምክንያት ሳይሳካ ቀርቶ በሰነድ መልክ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠ ።

እኛ በዓለም አቀፍ ተደራጅተን የምንገኝ የመዐሕድ ስራ አስፈፃሚ አባላት ይህ ታሪካዊ እድል ተሰጥቶን ዛሬ ስለ አማራው ህዝብ ሰብአዊ መብቶች ለመነጋገር እዚህ አዳራሽ ውስጥ በመገኘታችን ከፍተኛ ደስታ ይሰማናል ፤ ለተሰጠንም እድል በቅድሚያ እናመሰግናለን። አጭር መግቢያ፣ ባለፋት 27 ዓመታት በአገራችን ላይ ተንሰራፍቶ የነበረው ዘረኛው የህወሓት አገዛዝ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ከፍተኛ መከራና ስቃይ አድርሷል፤ በዘረኛው የህወሓት ቡድን የተጫነብንን የግፍ አገዛዝ ቀንበር አሽቀንጥሮ ለመጣል ብዙ መስዋእትነት የተከፈለ ቢሆንም በተባበረ የህዝቦች ክንድ በተለይም የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ልዩነታቸውን አስወግደው የጋራ ጠላታቸው የሆነውን ህወሓትን ለማስወገድ ያደረጉት ህዝባዊ አመፅ ዛሬ ያለውን የለውጥ ሂደት በር ለመክፈት ተችሏል። ነገር ግን ከፋፍሎ ለመግዛት እንዲያመቸው በዘረኛው የህወሓት ቡድን የተዘራው የዘር ጥላቻ መርዝ ከስሩ ተነቅሎ ባለመጣሉ ዛሬም በኢትዮጵያ ውስጥ ወገናችን የአማራው ህዝብ በማንነቱ መነሻ ከፍተኛ ኢሰብአዊና ዘግናኝ ወንጀሎች እየተፈፀሙበት ይገኛል። ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል ፣ በቤኒ ሻንጉል ፣ በአሶሳ ፣ በወለጋ ፣ በባሌ ጎባ ፣ እና በሌሎችም ስፍራዎች የአማራው ህዝብ እንደ አውሬ እየታደነ ይገደላል፤ ተወልዶ ካደገበት መንደርና ከእርስቱ እየተፈናቀለ ይባረራል፣ ህፃናትና ወላጆች ለረሀብ ለበሽታና ለሞት ተጋልጠዋል። …….ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።

 

Share this post