ከመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) የተሰጠ መግለጫ

ከመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) የተሰጠ መግለጫ

ጥቅምት 12 2010 ዓ.ም

በወገኖቻችን ላይ የተደረገውን ግፍ የተሞላበትንና ዘርን ያተኮረ ጭፍጨፋ እናወግዛለን!

ሰሞኑን በ”ኦሮምያ ክልል” ኢሊባቡር ደጋና ጮራ ወረዳዎች ከ20 በላይ ዐማሮችን ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ የቀጠፈውን ዘርን ተኮር ያደረግ ጅምላ ጭፍጨፋ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት በፅኑ ያወግዛል። በግፍ ከተገደሉት በተጨማሪም በሺዎች የሚቆጠሩ ዐማሮች ከጥቃት ለማምለጥ ከቤት ንብረቶቻቸው መፈናቀላቸውንና የደረሰውን ከፍተኛ የሆነ የንብረት ውድመትም ያወግዛል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በሸዋ ክፍለ አገር በመንግስት መለዮ ለባሾች የተፈጸመውን ግድያም መዐሕድ በፅኑ ያወግዛል።

አሁንም ቢሆን የአገዛዙ የፀጥታ ኃይሎች ለወገኖቻችን ተገቢውን ከለላ እንዲያደርጉ እየጠየቅን የጥፋቱን ፈጻሚ/አስፈጻሚዎችም ሆነ ከለላ ማድረግ ሲገባቸው ከለላ ያላደረጉ አካላት ከተጠያቂነት እነደማያመልጡ ልናስገነዝብ እንወዳለን።

በተፈጸመው አስቃቂ ግድያ የተሰማነን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን በሕዝባችን ላይ እጃቸውን ያነሱ አካላትን እስከ መጨረሻው እንደምንፋለማቸው ለማሳሰብ እንወዳለን።

የአማራ ሕዝብ በአማራነቱ የሚፈጸምበትን የአረመኔዎች ጭፍጨፋ በአንድነት በመቆም እንዲታገል ጥሪ ስናስተላልፍ መዐሕድ የአስተባበሪነቱን ሚና ከፍተኛ በሆነ ወገናዊነት ስሜት እንደሚወጣ በመግለጽ ነው።

ድል ለአማራ ሕዝብ!
መላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ)

 

Share this post