ከመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) የተሰጠ መግለጫ

መስከረም 20 ቀን 2010 ዓ.ም

ከመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) የተሰጠ መግለጫ

በፈረንጅ አቆጣጠር 9/30/2017 በዋሽንግተን ዲሲ ስለሚካሄደው
“የአማራ ድርጅቶች አቀራራቢ ኮሚቴ” ሰብሰባ የድርጅቱ ውሳኔ!

የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) የዐማራን ህዝብ ህልውና፣ መብትና ጥቅም ለማስከበር በማናቸውም ዐማራ የሚመለከቱ መድረኮች በመገኘት ይሳተፋል፤ ውጤቱንም ለህዝቡ ያሳውቃል፡፡ መዐሕድ ኢትዮጵያን ማእከል አድርገው ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ጋርም እንደ አስፈላጊነቱ የጋራ መድረክ መፍጠር ስለሚሚቻልባቸው ሁኔታዎች በሩ ክፍት ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ የዐማራ ድርጅቶችን ወይም ቡድኖችን ለማሰባሰብም ቅድሚያ ሰጥቶ ሲንቀሳቀስ የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ወደፊትም ይህንኑ ስራ አጠናክሮ ለመቀጠል ከመቸውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ዝግጁነቱን ያረጋግጣል፡፡ ከዚህ መሰረታዊ እሳቤው በመነሳትም መዐሕድ በ9/30/2017 በዋሽንግተን ዲሲ “የዐማራ ፓለቲካ ድርጅቶች አቀራራቢ ኮሚቴ” አማካኝነት “የዐማራ ድርጅቶችን ለማቀራረብ” በሚል አላማ በሚካሄደው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍም ሆነ ላለመሳተፍ የሁኔታውን አላማና መንፈስ በጥሞና ሲያጠና ቆይቷል፡፡ በጥናቱም ድምዳሜ መሰረት እየተካሄደ ያለው ጥረት የአማራን ሕዝብ ጥያቄ የማይመልስ፤ ከድርጅቱም አላማና መርህ ጋር የማይስማማ ሆኖ አግኝቶታል፡፡ በመሆኑም መዐሕድ በዚህ ጉባኤ ላይ እንደማይገኝ ያሳውቃል፡፡

ድል ለዐማራ ሕዝብ

መዐሕድ
read in pdf ስለ-ዲሲ-ጉባኤ-ኮሚቴ-መግለጫ

Share this post