የአማራ ህብረት በስዊዘርላንድ የአቋም መገለጫ

የአማራ ህብረት በስዊዘርላንድ የአቋም መገለጫ

16. 09.2017

ከውርደት ማህጸን የተወለዱት የአማራ ዘላቂ ጠላቶች ጫካ ሲገቡ የፈተሉት ፍኖተ- ርዕዮት አማራውን ጨርሶ የትግራይ ሪፐብሊክን ለመመሥረት ደደቢት ላይ የተፈለፈለ እንቁላል ከሁለት ነገር የተጸነሰ ነው። አንዱ ክህደት ሲሆን ሁለተኛው ዘርን መሠረት ያደረገ ጥላቻ ነው። ኢትዮጵያን እንደ ሀገር እና ዐማራን እንደማህበረሰብ አሟጦ ለማጥፋት።

“በውጡልኝ ከሀገሬ የፓለቲካ ፈሊጥ“ ጭራቃዊ ግፍ እና አማራ የማስወገድን የጥፋት ዘመቻ በወበራነት የከፈተው የትግራይ ወያኔ ከ 100, 000 በላይ ሲያፈናቅል ከ6 ሚሊየን በላይ ደግሞ አጥፍቷል። እርጋፊ የሀገር ፍቅር ያልፈጠረባቸው የባንዳ ልጆች ሞትን እንደምርት ቆጥረው ለቅሶን እንደሥራ የቀየረው የአማራ ህዝብ ምን ይደርስብኝ ይሆን በማለት ስጋው በስጋት አልቆ አንጀት በሚያ ላውስ የመኖር እና ያለመኖር ጥያቄ ቀጣይ ምጽአቱን ይጠብቃል። ጥልቀት ባለው ብሶት የሰመጠ እና የስርአታዊ ምሬቱን የመጨረሻ ጽዋ አንጠፍጥፎ የጨለጠው ሕዝብ ከእሳተጋሞራ የሚልቅ እንደአቶን የሚንቀለቀል የቁጣ ስሜት ስለማርገዙ የጭንቀት እንቧ ላም ድምጽ ሆኖ ያሰማል።

የኢትዮጵያዊነት መሠረቱ እና ጽናቱ በወያኔ ዘመነ አገዛዝ ድውይ ፕሮፓጋንዳ እና እኩይ ምግባር ለይቶለት በጎጥ በሽታ እየተፈጠ ፈጠ ተንዷል። በጎሳ የሚገነፋው የወያኔ ፖለቲካ በቶሀን እንደተወረረ ገላ አማራውን እያንገበገበ የሚገኘው ኢትዮጵያ ባለመኖሯ ነው። በ 9 ክልሎች ተሸንሽና የዘረኝነት ፖለቲካ በኢትዮጵያ ላይ ያጠለቀው ገመድ የታነቀች ኢትዮጵያን እንድንመለከት በማድረጉ ነው። በጋራ ተነስተን በወያኔ ጭካኔ እና ክፋት ልክ የሆነ ተጋድሎ ያላደረግነው ጅብ እንዳገኘው የአህያ ገላ አገር ስለፈረሰች ነው። ….. ( Continue Reading, pdf )

 

Share this post