የመጀመሪያው የአማራ አለማቀፍ ጉባኤ ፕሮግራም (ግንቦት 6/2009 ዓ.ም) The First Amhara International Conference (14th May 2017)

የመጀመሪያው የአማራ አለማቀፍ ጉባኤ ፕሮግራም (ግንቦት 6/2009 ዓ.ም) The First Amhara International Conference (14th May 2017)

የቀዳማዊ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት ምስረታ 25ኛ አመት ኢዩቤልዩ ክብረ በአል፣ የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ 18ኛ ሙት አመት መታሰቢያ እና የዳግማዊ መዐሕድ 2ኛ አመት እንደገና ምስረታ በአል ሜይ 14 ዓ.ም 2017 በዋሽንግተን ዲሲ ይካሄዳል። ይህም ጉባኤ የመጀመሪያው የአማራ አለማቀፍ ጉባኤ ተብሎ ይጠራል። ጥቅል የጉባኤው ምንነት፣ አላማና ግብ እንደሚከተለው ተቀምጧል።

1. የጉባኤው አላማ

1.1. የአማራው ህዝብ ለወገኑ ተሰባስቦ ዘላቂ መፍትሄ እንዲቀይስ ማስቻል
1.2. ልዩ ልዩ አማራን የሚመለከቱ ሰነዶች እንዲቀርቡና ለህዝቡ በታግሎ ማታገያነት እንዲደርሱ ማድረግ።
1.3. የአማራው ሕዝብ ለመጭዎቹ ትውልዶች ፈር የሚሆነውን አለማቀፍ ጉባኤ በማድረግ የአማራ አለማቀፍ ትግል ዋና መሪ መሆኑን ማረጋገጥ።

2. የጉባኤው ጥቅም

2.1. ለአማራ ህዝብ ችግሮችን እና መፍትሄዎችን በተመለከተ ሰነዶችን ማዘጋጀት
2.2. አማራን ማሰባሰብ እና ስለራሱ እጣ ፋንታ እንዲመክር ማድረግ
2.3. በውጭ ያለው አማራ በአገር ውስጥ መከራ ለሚወርድበት ወገኑ አለኝታውን በአንድነት በመቆም እንዲያሳይ ማድረግ
2.4. የአገር ውስጡን ትግል ለመደገፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ማድረግ
2.5. የአማራውን ድርጅታዊ ህልውና ማጠናከርና ሁሉንም አማራ የትግሉ ተሳታፊ የሚሆንበትን መንገድ መቀየስ

3. የጉባኤው ተሳታፊዎች

3.1. ማንኛውም አማራ የሆነና ስለአማራ ያገባኛል የሚል ሁሉ በጉባኤው ይገኛል
3.2. የአማራ ምሁራን እንዲሁም ሌሎች ስለአማራ ጥናት ያደረጉ የውጭ ምሁራን ጽሁፍ ያቀርባሉ
3.3. የአማራ ድርጅቶችና ማህበረሰባት መሪዎች ጽሁፍ ያቀርባሉ።

4. የጽሁፎች ጥቅም

4.1. በጉባኤው የሚቀርቡት ጽሁፎች ከጉባኤው በኋላ በመጽሀፍ መልክ ታትመው ለህዝብ እንዲደርሱ ይደረጋል።
4.2. ይህም ሰነድ የአማራ ህዝብ ታግሎ ማታገያ ሰነድ ማለትም የህዝቡን የረዥም ርቀት ግብ የሚያመለክት ሰነድ ይሆናል።
4.3. ከሚታተመው መጽሀፍ የሚገኘው ገንዘብ የአማራውን ትግል ለማገዝ ይውላል።

5. የጽሁፎች ርእሶች

(በተዘረዘሩት ረእሶች በቀጥታ የተገናኘ ብቻ ሳይሆን በእነዚሁ ርእሶች ዙሪያ የሆነ ማንኛውም ጽሁፍ ተቀባይነት ይኖረዋል። በሚታተመው መጽሀፍ ውስጥ እስከ 30 የሚደርሱ ርእሶች ሊካተቱ ይችላሉ።)

5.1. አማራ ማን ነው? ከታሪክ፣ ፖለቲካ፣ ባህል፣ ቋንቋ እና አጠቃላይ ማንነት ጋር በተገናኘ የሚደረጉ የምርምር ጽሁፎችን ያካትታል።
5.2. አማራ እና ኢትዮጵያ፡- አማራ ለኢትዮጵያ እንደ ልጅነት እና ኢትዮጵያ ለአማራ እንደ እናትነት ዝርዝር ሁኔታ ይቀርብበታል።
5.3. የአማራ ሁለንተናዊ ህልውና አደጋ ውስጥ ነው ስንል? በአማራው ላይ የተጋረጡ ልዩ ልዩ የህልውና ፈተናዎች ከነመፍትሄዎቻቸው ይቀርቡበታል።
5.4. አማራና ምጣኔ ሀብታዊ ይዞታው፡ ትላንት ዛሬ እና ነገ።
5.5. አማራ እና ፖለቲካዊ ውክልናው እንደ ወርድና ቁመቱ። ትላንት ዛሬ እና ነገ።
5.6. የአማራ ታሪካዊ የግዛት ድንበሮች ታሪክና ዝርዝር ማስረጃዎች።
5.7. የወደፊቷ በእኩልነት ላይ የምትመሰረተው ኢትዮጵያ እንደ አማራ ፍላጎት ከዳግም ጥፋት ለመዳን ሲታሰብ።
5.8. የአማራን ሁኔታ በኢትዮጵያ እጣ ፋንታ ላይ ለክፉውም ለበጎውም በእንዴት ያለ ሁኔታ ተዘጋጅቶ መጠበቅ ይኖርበታል? በዚህ ውስጥ የአማራን ቀጣይ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ተጨባጭና ተለዋዋጭ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ ህዝቡ በምን በምን ረገድ የስነልቡና ዝግጅት አድርጎ መጠባበቅ እንዳለበት የሚያዘጋጁ ጽሁፎች ይቀርቡበታል።

6. የጽሁፎች ሁኔታ

6.1. በመጀመሪያ ተሳታፊዎች አንድ ገጽ ብቻ መሪ ሀሳብ (አብስትራክት) መላክ ይጠበቅባቸዋል። መሪ ሀሳቦች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ በአንድ ሳምንት ውስጥ መላክ ይጠበቅባቸዋል።
6.2. መሪ ሀሳቡ በአዘጋጆች ከተመረጠ በኋላ ለተሳታፊዎች ይላካል።
6.3. ዋናው ወረቀት ከ15-30 ገጽ መሆን ይገባዋል።
6.4. ተሳታፊዎች ከ10-15 ደቂቃ ገለጻ ያደርጋሉ፤ከ5- 10 ደቂቃ የጥያቄና መልስ ጊዜ ይኖራል።
6.5. ተሳታፊዎች ዋናውን ጽሁፍ ጉባኤው ከመደረጉ ሁለት ሳምንታት በፊት መላክ ይጠበቅባቸዋል።
6.6. ጽሁፎች በመጽሀፍ መልክ ስለሚታተሙ ከፍተኛ ጥራት እንዲኖራቸው ይጠበቃል፤ በማስረጃ እና በተገቢው ማጣቀሻ ምንጮች መታገዝ ይጠበቅባቸዋል። ምንጭ የሌለው ጽሁፍ ለመታተም ብቁ አይሆንም።
6.7. አጠቃላይ የጽሁፎች ይዘት የአማራን ህዝብ ወቅታዊ ችግር እየዳሰሰ መፍትሄ ጠቋሚ ቢሆን ይመረጣል።

7. የተሳትፎው ሁኔታ

7.1. ጽሁፋቸው የተመረጠላቸው በአካል በመገኘት ገለጻ ያደርጋሉ።
7.2. በአካል መገኘት የማይችሉ ጽሁፎችን በመላክ በሚታተመው መጽሀፍ እንዲካተትላቸው ይደረጋል።

ጽሁፍ አቅራቢዎች የሚከተለውን የድርጅቱን ኢሜይል አድራሻ መጠቀም ይገባቸዋል።

ዝግጅቱን ለማገዝ የሚፈልጉ የአማራ ድርጅቶችና ማህበራትም ይሄንኑ አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።

aapo2nd@gmail.com

ለበለጠ መረጃ የድርጅቱን ድረ-ገጽ http://www.aapo2nd.org/ ይመልከቱ

ዳግማዊ መዐሕድ

Share this post