እንደ በለሴውም ሆነ እንደ ወገሬው፤ እንደ ፋርጣውም ሆነ እንደ መንዜው፤ እንደ አገውም ሆነ እንደ ወልቃይቴው – ቅማንትም አማራ ነው፤ በቅማንት ላይ የሚደርስ ጉዳት በአማራ ላይ የሚደርስ ጉዳት ነው! ከዳግማዊ መዐሕድ የተሰጠ መግለጫ

እንደ በለሴውም ሆነ እንደ ወገሬው፤ እንደ ፋርጣውም ሆነ እንደ መንዜው፤
እንደ አገውም ሆነ እንደ ወልቃይቴው – ቅማንትም አማራ ነው፤
በቅማንት ላይ የሚደርስ ጉዳት በአማራ ላይ የሚደርስ ጉዳት ነው!

የዐማራ ሕዝብ፤ በብዙ ዘርፍ የዘር ግንድ የተገነባ፤ ተመሳሳይ የሆነ ስነልቡና፣ ወግ፣ ልማድ፣ ባህልና ቅርስ በውልጠት ያበለጸገ ሕዝብ ነው። አንዳንድ ጊዜ አሁን በብዛት በሚኖርባቸው መልክዓ ምድር ጎጃሜ፣ ጎንደሬ፣ ሸዌ፣ ወሎዬ በሚል የተለምዶ አጠራር ሲታወቅ በተጨማሪ ደግሞ ማህበራዊ ውልጠት ቋንቋን በተለየ ባሳደገበት አካባቢ ቅማንት፣ አገው፣ አርጎባ፤ ወይጦ፤ ቤተ እስራኤል ወዘተ በመባል ይታወቃል። በመልክአ ምድርም ሆነ በቋንቋ ማንነቱ የሚገለጸው ዐማራ ከአንድ የዘር ግንድ ቅርንጫፍ የተፈጠረ እንጅ ምንም ዓይነት መሰረታዊ የስነልቡና ልዩነት በመካከሉ እንደሌለ ቢታወቅም፤ ራሱ ዐማራው ሳይሆን ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚቋምጥለትን የታላቋ ትግራይ ተስፋፊ አላማ ለማሳካትና አላማውን በተከታታይ ያከሸፈበትን ጀግና የዐማራ ህዝብ ለመከፋፈል፣ ለማዳከምና ለመበቀል፤ ለራሱ ጥቅም ሲል ሰው ሰራሽ ልዩነቶችን በመፍጠር በዐማራው የህልውና ተጋድሎ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ለመቸለስ አሁንም የተለመደውንቅማንትና ዐማራ ብሎ የመከፋፈል ዕኩይ ስራውን መጀመሩ የአደባባይ ሚስጥር ነው።

ለዘመናት በደም ተሳስሮና ተዋህዶ፤ አገሩን በጋራ ከወራሪም ሆነ ከውስጥ ጠላት ተከላክሎ፤ ለረዥም ዘመናት በተለምዶ መኖሪያወቹም ሆነ ከዚያም ወጣ በማለት በመላ ኢትዮጵያ ተሰማርቶና ተሰባጥሮ የሚኖረው ዐማራ እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የደረሰበት ግፍ አልበቃ ብሎ ዛሬ እንደ አንድ ሕዝብ የህይወቱ ቅድስና፤ የንብረቱ ባልቤትነት ተከብሮለት በነጻነት የመኖርና የመቀጠል መብቱ በመገፈፉ፤ የሞት ወይም የሽረት፤ የህልውናና ሉዓላዊነት ትግል ውስጥ ይገኛል። ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ በዐማራው ሕዝብ ላይ ይህ ነው የማይባል ዕልቂት፣ ግፍና በደል እየፈጸመ ይገኛል። ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ሊያጠፋው የሚፈልገው የዐማራው ዘር (ወገሬውን፤ ፋርጣውን፣ በለሴውን፤ መንዜውን፤ ጣቁሴውን፣ ደምቤውን፤ ጋይንቴውን፤ ዳሞቴውን፤ ላኮመንዛውን፤ ላስቴውን፤ ሰቆጤውን፣ ቅማንቱን፣ አገውን፣ ቡልጌውን፣ ሸንኮሬውን፤ ይፋቴውን ወዘተ..) መሆኑን በግልጽ አውጆ ዛሬ በከባድ መሳሪያና በብዙ ጦር በመውረር በጅምላ እያስጨነቀ፣ እያሰረ፣ እየረሸነ፣ እየጨፈጨፈ፣ እያሳደደና እያንገላታ፣ ቁም ስቅሉን እያሳየው ይገኛል።

አሻፈረኝ ባዩ፣ ለነጻነቱ ቀናዒ የሆነው የዐማራ ሕዝብም ከአያት ቅድመ አያቶቹ የወረሰውን ጀግንነት ስንቁ አድርጎ፣ ለነጻነቱና ለህልውናው በቆራጥነት፤ በጁ በያዘውና አቅሙ በሚፈቅደው ሁሉ በቅማንት፣ በአገው፤ በበለሳ፤ በወገራ፣ በሰሜን፤ በወልቃይትና ጠገዴ ዐማራ ጎበዝ አለቆችና ጀግኖች ልጆች መሪነት እምቢ እያለና እየተፋለመ ይገኛል። ከመተማ እስከ ደሴ፣ ከደባርቅ እስከ ደብረ ማርቆስ፤ በእያንዳንዷ ከተማ፣ ቀበሌ፣ ወረዳና አውራጃ የደም ግብር እየከፈለ ይገኛል። …..Read more, pdf

Share this post